Wednesday, 17 June 2015



 
the men's and females' dormitory
          

የወንዶች እና የሴቶች ዶርም ፊት ለፊት በመሆኑ ሴት ተማሪዎች መቸገራቸዉንገለፁ         
         

BySelamawitDebebe                                                                                                                                                                       

  በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አዲሃቂ ግቢ ህዳር ወር ላይ ተከስቶ በነበረዉ የወንዶች ዶርም የእሳት ቃጠሎ ምክንያት  ወንድ ተማሪዎች የሴቶች ዶርም ፊት ለፊት በሚገኘዉ ህንጻ ላይ ማረፊያ ተሰጥ~ቸዉ እንደነበር ይታወሳል$

 ወንድ  ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ዉሃ በመድፋት እና የተለያዩ አፀያፊ ስድቦችን በመሳደብ እና 
  በመላከፍ እንዳስቸገVቸው ከሴት ተማሪዎች መረዳት ችለናል$ በዚህም ምክንያት ሴት ተማሪዎች እንደልባቸው
 መዉጣት እና መግባት አልቻልንም ብለዋል$

ያነጋገርኩዋቸዉ ሴት ተማሪዎች ችግሩ እንዲፈታ ፍላጎታቸዉ እደሆነም አክለዉ ገለፀዋል$ በተለያየ ጊዜ ይሄን ድርጊት በፈፀሙ
ተማሪዎች ላይ ርምጃ እንደተወሰደ አንዳንድ የገቢዉ የጥበቃ ሰራተኞች ቢገልፁም ይህ ነዉ የሚባል የተፈታ ችግር አልታየም$

የሴት ተማሪዎችን መብት ለማስከበር የሚሰራዉ የመቀለ ዩኒቨርሲቲ የስነ ፆታ ፅህፈት ቤት  እዚህ ላይ ምን አይነት ስራዎች
 እየሰራ እንደሆነ ጥያቄ ዉስጥ የሚገባ ነገር ነዉ$

ይህ የሴት ተማሪዎችን መብት የሚነካና ድርጊቱን ለማስቆም ብሎም ይህን ድርጊት በሚፈፅሙ ወንድ ተማሪዎች ላይ የቅጣት ርምጃ ለመዉሰድ የግቢዉ የተማሪዎች ፖሊስ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል$

No comments:

Post a Comment