Thursday, 18 June 2015


                  የመጨረኛዋ ሰአት

የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ተ ማሪ ዎች በ ስ ራ ላይ


by Selamawit Debebe
 
ጊዜዉ ተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ ፅሁፋቸውን የሚያቀርቡበት እንደሆነ ይታወቃል᎓᎓
ታዲያ ተማሪዎቹ የመመረቂያ ፅፋቸዉን የሚያቀርቡበትን ሰአት በጉጉት እና በፍርሃት ይጠባበቃሉ᎓᎓
ለሚለብሱት ሲጨነቁ እና
እንዴት ፅሁፋቸዉን እንደሚያቀርቡ ሲለማመዱ ይቆያሉ᎓᎓በነዚህ በመጨረሻዎቹ ቀናት የተሰጣቸዉን ስራ ለመስራት አምሽተዉ ካልሆነም አንግተዉ ያጠናቅቃሉ᎓᎓
ይህም ለነሱ  ልምድ እና ትምህርት እንደሚሆናቸዉ ተናግረዋል᎓᎓

የጆርናሊዝምና ኮምኒኬሽን ትምህርት ክፍል ተመራቂ  ተማሪዎችም የመጨረሻ አሳይመንታቸዉን ለመስራት ለሊቱን በሙሉበስራ አንግተዋል᎓᎓
የቪዲዮ ፕሮዳክሽን አሳይመንታቸዉን ለመስራት ተፍ ተፍ ሲሉ ያመሹት ተመራቂ ተማሪዎች ለሊቱን ሙሉ
እንቅልፍ በአይናቸዉ ሳይዞር እንዳደረሩ በግርምት ተናግረዋል᎓᎓ 
እንቅልፍ የጣላቸዉንም ተማሪዎች በየወንበሩ ጋደም ብለዉ
ታይተዋል ሆኖም ግን ተማሪዎቹ የማይረሳ ትዉስታን እንዲሁም ልምድ ያገኘንበት ነዉ ብለዋል᎓᎓

የጋዜጨኝነት ስራ ምን እንደሚመስል እና የሚያጋጥመዉን መሰናክል ካየንበት ሂደቶች መካከል አንዱ ነዉ ብለዋል᎓᎓



No comments:

Post a Comment