Tuesday, 16 June 2015



                      
                           ፒፒሲ በአዲስ መልክ ስራ ጀመረ
በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ  አዲ ሃቂ ግቢ በተለምዶ ፒፒሲ እየተባለ የሚጠራው የተማሪዎች መዝናኛ በ አዲስ መልክ ስራ ጀመረ 
 By Selamawit Debebe
መዝናኛው የተለያዩ ማሰሻሻዮች ተደርገውበታል ከ እነዚህም መካከል  የምግብ አገልግሎት እና ልዩ ልዩ  ቁሳቁሶች ይገኙበታል እንዲሁም የተለያዩ አትክልቶችን የመትከል  እና ሳቢና ማራኪ የማድረግ ስራዎች  እየተሰሩ መሆናቸውን ያነጋገርኳው የ መዝናኛው ሰራተኞች ገልፀውልኛል። 
 
በተጨማሪም በ አዲሰ መልክ ስራ መጀመር ብቻ ሳይሆን ስሙንም በመቀየር ጎጆ መዘናኛ ተብሏል ያነጋገርኳው ተማሪዎች በመዝናኛው አገልግሎት እንደተደሰቱና በተለይ የወተት አቅርቦቱ  
እንደተመቻቸ ገልፀውልኛል።
The new view of PPC
ይህ መዝናኛ ግቢ ውስጥ ካሉት ሌሎች መዝንኛ እንደ አማራጭ መቅረቡ የተማሪዎችን ፍላጎት ከማሟላት አኳያ መልካም የሚባል ነው።

 መዝናኛውም እንደ እቅድ ለወደፊቱ ተጨማሪአገልግሎቶችን ለመሳቅረብ እንዳሰበ ካነጋገርኳቸው ሰዎች ለመረዳት ችያለው። 
 
የመዝንኛውን ሀላፊ ስለስያሜው ጠይቂያቸው ጎጆ መዝናኛ የተባለበት ምክንያት የጎጆ ቅርፅ ስላለው እንዲሁም ባህላችንን ለመግለፅ እንደሆነ ነግረውኛል። 
በተያያዝ ዜና ግቢውን የማስዋብን የማፅዳት ስራ እየተሰራ ይገኛል። 
 አብዛኞቹ ተማሪዎች የመዝናኛ እጥረት እንዳለ ይገልፃሉ። ይህ መዝናኛ መከፈቱ ደግሞ ተማሪዎቹን ላማራጭ መዝናኛ ሌላ ቦታ እንዳይሄዱ እና ገንዘባቸውን እንዳያበከኑ አግርጓቸዋል።  


No comments:

Post a Comment