by Selamawit Debebe
ድንኳኑ በተማሪዎች መመገብያ ካፌ በሰልፍ ሰዓት
ተማሪዎችን ከጸሃይ ለመከላከል ተብሎ የተሰራ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ
መሆኑ ግን ተማሪዎችን አስቆጥቷል።
በዓዲ ሃቂ ግቢ የካፌ ሃላፊ የሆነዉ
አቶ ተስፋየ ገ/ሚካኤል እንደተናገረዉ ድንኳኑ እንዲሰራ ከጠየቅን ቆይተናል ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዉን ምላሽ መጠበቅ ስለነበረብን
ወደ አመቱ መጨረሻ ልንመጣ ግድ ሆኖብናል ብሏል።
ያነጋገርናቸዉ አንዳንድ ተማሪዎች እንደተናገሩት
ይሰራላችኋል ተብሎ ከሰባት ወር በኋላ መድረሱ እጅግ አሳፋሪ ነዉ ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የድኳኑ መሰራት ለቀሪ ተማሪዎች ሊያገለግል
የሚችል ቢሆንም ከግቢ ለሚወጡ ተማሪዎች ግን ምንም ፋይዳ የለዉም ሲሉ
ተመራቂ ተማሪዎች ተናግረዋል።
የድንኳኑ መሰራት የተማሪዎቹን ፍላጎት ያላሟላ
ከመሆኑም በተጨማሪ ሊሰጥ ስለሚችለዉ አገልግሎት ግን ሌላ ጥያቄ በተማሪዎቹ
ተነስቷል። ለጥላ ተብሎ የተዘረጋዉ ሸራ በቂና ጥንካሬ የሌለዉ ነዉ።
እነዚህና መሰል ጉዳዮች የተማሪዎቹ ጥያቄ ሆነዉ ምላሻቸዉ ቢሮ
ክራሲ የበዛባዉ ናቸዉ ተብሏል። ከ5000 በላይ ተማሪዎች የካፌ ተመጋቢ መሆናቸዉ የሚታወስ ነዉ።
No comments:
Post a Comment